2013 ኤፕሪል 10, ረቡዕ

+++++++++ኦርቶዶክስ ተዋህዶ +++++++++

 +++++++++ ተዋህደ ስንል ምን ማለት ነው? +++++++ ያ ቅድመ አለም ከአብ ዘንድ የነበረው ወልድ/ቃል/ ከድንግል ከስጋዋ ስጋን ከነፍሷ ነፍስን ነስቶ ተወለደ። የሐ.1፤14 ያ ቃል ስጋ ሆነ። እንዲል። ቃል ስጋ ሆነ ሲባል ተለዉጦ ስጋ የሆነ አይደለም በቃና ዘገሊላ ወሓው ወደ ወይን ተጅ እንደተለወጠው ቃል ወደ ስጋነት አልተለወጠም። ወይም በልብስ ላይ ልብስ እንደሚለበሰው በቃል ላይ ስጋ አልተደረበበትም። መለኮትም ስጋን አላጣፋውም ስጋም መለኮትን አልዋጠውም።አንድ ብረት በእሳት ውስጥ ቢጨመር ብረቱ ቅርጹን ሳይለቅ የእሳትነትን ባህርይ እንደሚይዝ ስጋ የመለኮትን ባህርይ ገንዘብ አደረገ። እሳቱ በብረቱ በማደሩ ቅርጽ እንደሚወጣለት መለኮት ከስጋ ጋር በመዋሀዱ ታየ ተዳሰሰ ተኛ ተነሳ ተባለ።ይህ የወልድ ሰው መሆን ምስጢር ታላቅ ነው። እንደምስ የረቀቀ ነው።ሐዋርያው ለዚህ ነው ይህ ሚስጢር ታላቅ ነው። እግዚአብሔርን መምስል ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው ያለው።1ኛጢሞ 3፤17 ዓለም የዳነው በተዋህዶ ነው። የኢየሱስ ክርስቶስ ተዋህዶን ለማብራራት የሚከተለውን የክርስቶስ ትምህርት እንውሰድ፡ እውነት እውነት እላችሗለሁ ስጋየን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘለዓለም ህይወት አለው። ዮሐ 6፤55 ይህ ቃል እንዲሚያስረዳን ስጋውና ደሙ የዘለዓለም ህይወትን ለማግኘት ወሳኝ መሆኑን ነው። ታዲያ ስጋውና ደሙ ከማርያም የተገኘ የሰው ስጋ ነው። የሰው ስጋ ደግሞ ብቻውን ሊያድን አይችልም ኢንዲያውም ሊያም ይችላል። መለኮት ደግሞ ስጋ የለውም። ስለዚህ ይህ ስጋና ደም በተዋህዶ የከበረ ነው እንላለን። ስጋን መለኮት ስለተዋሀደው አዳኝ አደረገው። መለኮት ስጋን ስለተዋሀደው የሚዳሰስ የሚጨበጥ አደረገው። በመሆኑም በተዋህዶ የከበረ ስጋውና ደሙ መዳኛ ሆነ።

2013 ኤፕሪል 3, ረቡዕ

‹‹ ተው ስማኝ ሀገሬ.. . .››

‹‹ ተው ስማኝ ሀገሬ.. . .››

 

‹‹ ተው ስማኝ ሀገሬ.. . .››
አረ ስማኝ ሀገሬ. . .ተው ስማኝ ሀገሬ
አረ ስማኝ ሀገሬ. . .አረ ስማኝ ሀገሬ


                በጌቲ ሠማኔ ባታክልቱ ቦታ
                ለኛ ሲል ጌታችን በዓለም ተንገላታ. . . . . . . በዓለም ተንገላታ
አዳምና ሔዋን. . . ባጠፉት ጥፋት
እኛም ነበረብን የዘለዓለም ሞት. . . . . . . . . . . የዘለዓለም ሞት

               መስቀል ተሸክሞ. . . ሲወጣ ተራራ
               ይገርፉት ነበረ ሁሉም በየተራ. . .  . . ሁሉም በየተራ

አሳ አትብሉ. . .  ብሎ ቄሱ ሲራገም

አሳ’ማ ይበላል በሁዳዴ ፆም. . . . በሁዳዴ ፆም
            
               አረ ስማኝ ሀገሬ. . .  አረ ስማኝ ሀገሬ
               አረ ስማኝ ሀገሬ. . .  አረ ስማኝ ሀገሬ
የተጠበሰ አሳ ይሸታል. . . .እጃችሁ
አረ እናንተ ሠዎች አሳ’ማን በላችሁ. . . አሳ’ማን በላችሁ
              መለስ ቀለስ ብላ. . . አየችው ቀሚሷን
              እረሳችውና ካፈር መለወሷን. . . በአፈር መለወሷን
አረ ስማኝ ሀገሬ. . .  አረ ስማኝ ሀገሬ
አረ ስማኝ ሀገሬ. . .  አረ ስማኝ ሀገሬ
              
              በስምንተኛው ሺህ . . . በተልከሠከሠው
              ቤተስኪያን ይስሟል አይጣሉም ከሠው. . . አይጣሉም ከሠው
ሠርቼ ሠርቼ. . . አዳራሽ ከ’ልፍኝ
በማለቂያው ጊዜ ላፈርሰው ሆንኩኝ. . . ላፈርሰው ሆንኩኝ
              እስከዛው ድረስ ነው. . .  ሲሶ ማረሳችን
              እንገባ የለም ወይ በየመሬታችን. . . . በየመሬታችን
ጎድን ከዳዊቱን. . . ተፍትፈህ ጥበሰው
እስኪበላ ሞቱን አያውቀውና ሠው. . . አያውቀውና ሠው
              
              አረ ስማኝ ሀገሬ. . .  አረ ስማኝ ሀገሬ
              አረ ስማኝ ሀገሬ. . .  አረ ስማኝ ሀገሬ
ሠው ከሶኛል አሉ. . .ቆሞ አደባባይ
እውነት ነውር ሆኖ. . . ሊያስቀጣኝ ነው ወይ. . . ሊያስቀጣኝ ነው ወይ
              ሸንበቆ ግድግዳ. . . ማገር ከመቁረጥ
              መዘን ቤት ይሰራል የማይናወጥ. . . የማይናወጥ
አረ ስማኝ ሀገሬ. . .  አረ ስማኝ ሀገሬ
አረ ስማኝ ሀገሬ. . .  አረ ስማኝ ሀገሬ
              ሸማኔው ሠውዬ. . . ችግር ሳይገባው
              አንድ ሀርብ ቢኖረው ለስጋ ሸጠው. . . ለስጋ ሸጠው
አረ ስማኝ ሀገሬ. . .  አረ ስማኝ ሀገሬ
አረ ስማኝ ሀገሬ. . .  አረ ስማኝ ሀገሬ
              ጣናን በታንኳ ላይ ሲጓዙ ስታይ
              አረ አባይን በግር ትጓዛለህ ወይ. . . ትገባለህ ወይ
አረ ስማኝ ሀገሬ. . .  አረ ስማኝ ሀገሬ
አረ ስማኝ ሀገሬ. . .  አረ ስማኝ ሀገሬ

2013 ኤፕሪል 2, ማክሰኞ

‹‹የገሀነም ደጆች አይችሏትም››

‹ቤተክርስትያኒቷ ትዘጋ›› የሚል ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ


‹‹የገሀነም ደጆች አይችሏትም››
ጊዜው ወርሀ ክረምት ነው :: የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ፆመ ፍልሰታ ወቅት ሲሆን በቤተክርስትያናችን ህግና ስርዓት መሰረት ይህ ጊዜ ዲያቆናት ፤ ካህናት መነኮሳት ፤ ጳጳሳት እና ምእመናን ለሐዋርያት የተገለፅሽላቸው እናታችን ለእኛም በምህረት አትለይን እያሉ በፆም ፤ በፀሎት ፤ በስግደት የሚለምኑበት ጊዜ ነው፡፡

ቦታው በሐረር መንገድ አዋሽ ሰባትን አልፈው ካለው የጉምሩክ የፍተሻ ጣቢያ ትንሽ ኪሎ ሜትር አለፍ ብሎ ከአሰቦት ገዳም መገንጠያ ሳይደርስ ከዋናው አስፋልት አንድ ኪሎ ሜትር ላይ የሚገኝ የአባታችን የአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ቤተክርስትያን ሲሆን የቦታው ስም ቦርደዴ በመባል ይታወቃል፡፡ ይህ ቤተክርስትያን የሚገኝበት ቦታ ላይ ከ30 የማይበልጡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞች ሲገኙ በቁጥር ከ40 እና ከ50 እጥፍ ልቀው የሚገኙት ግን ሙስሊም ማህበረሰቦች ናቸው፡፡ ይህ ቦታ ለአንድ አፍታም ቢሆን ከነገር እና ከትንኮሳ እፎይ ያለበት ጊዜ የለም፡፡ ቦታ ድረስ ሄጄ በተመለከትኩበት ጊዜ እዚህ ቦታ ላይ ያለው የሙቀት መጠን ክረምት ሳይል በጋ ከ40 ድግሪ በላይ ስለሆነ ቆሞ ማስቀደስ እንደ እግዚሐብሔር መልካም ፍቃድ ፤ ምህረት ፤ ቸርነት እንጂ እንደ እኛ ብርታትና ጥንካሬ እንዳልሆነ ተረድቻለሁ፡፡

ቤተክርስትያኒቷ አካባቢ ያሉት ምዕመና ጧፍ ፤ እጣን ፤ ዘቢብ እና ንዋየ ቅዱሳትን ማሟላት አቅሙ ስለሌላቸው ይህ ችግር የቀን ተቀን የውስጥ ችግር ችግራቸው ሆኖ አሁንም አሉ ፡፡ የባሰ አታም ነውና  አንድ ጊዜ ቅዳሴ ላይ ወንጌል ለማንበብ ጧፍ አልቆ በኩራዝ የተጠቀሙበት ጊዜም ነበር ፡፡
በአካባቢው የሚገኙ ከአክራሪ ወገን የሚመደቡት የእስልምና ተከታዮች በአካባቢው ላይ ለ24 ሰዓት ያህል ከ4 በሚበልጡ መስኪዶቻቸውን ድምፅ ማውጫ Speaker ወደ ቤተክርስትያን አዙረው ‹‹አላህ ዋክበር›› በሚሉበት ሁኔታ ላይ ምንም ጥያቄ ያላቀረቡት በአካባቢው የሚገኙ  ክርስትያኖች በዓመት አንድ ጊዜ ለ16 ቀናት ብቻ ያለውን የሱባኤ ጊዜ ለሊት ሰዓታት እና ኪዳኑ ፤ ጠዋት ትርጓሜው እና ስብከቱ ፤ ከሰዓት ቅዳሴው ረበሸን ብለው ቤተክርስትያኒቷ እንድትዘጋላቸው  ለአካባቢያቸው ወረዳ አስተዳደር ሰላማዊ ሰልፍ አድርገው መጠየቃቸውን አረጋግጠናል፡፡ ይህን ጥያቄ የመስተዳድሩ  ሃላፊ ከሰማ በኋላ ለሚቀጥለው ቀን የቀጠራቸው ሲሆን በሚቀጥለው ቀን ሲመጡ ምንም ምላሽ ስላላገኙ ሓላፊውን በኃይል ከቢሮ ያባረሩት ሲሆን ፡፡ ይህ ጥያቄያቸው የክልሉ መንግስ ጋር እንደደረሰ ፤ አካባቢው ላይ የሚገኙ ክርስትያኖች ጉዳዩን ወደ ፊደራል መንግስት የወሰዱት ሲሆን መንግስት የዛኑ ቀን ማታ አካባቢው ላይ የሚገኙ ፌደራል ፖሊሶች ማታ 3፡00 አካባቢ ወደ አካባቢው በፓትሮል በመምጣት ይህን ጥያቄ የጠየቁትን ሰዎች ግማሽ ያህሉን ለቅመው ወስደው ወደ እስር ቤት የከተቷቸው  ሲሆን የተቀሩትን ግን ሸሽተው አምልጠዋል፡፡ መንግስት ይህን እርምጃ ከወሰደ በኋላ ሁኔታውን በጥቂቱ ያረጋጋ ሲሆን ፡፡ በአሁኑ ወቅት አካባቢው በፊደራል ፖሊስ  እየተጠበቀ ይገኛል::

እኛ በአሁኑ ሰዓት እንትና 18 ገፅ ወቀሳ ፃፈ ፤ ያኛው ሰባኪ አውደ ምህረት ላይ እንዳይቆም ተከለከለ ፤ በዚህ መፅሄት ላይ እንትና መልስ ሰጠ ፤ አንዱ ይቅርታ አለ ሌላኛው ይቅርታ ተቀበለ እያልን ስራ መስራት በሚገባን ወቅት ወሬ ስናራግብ ለቤተክርስትያን መሆን በሚገባን ሰዓት ጊዜያችንን እና አቅማችንን አልባሌ ቦታ ላይ በማዋልና ትርፍ የሌለው ስራ በመስት ላይ እንገኛለን፡፡

አሁንም ጊዜው አልረፈደም ስለ ጥቂት ሰዎች ማውራታችንን አቁመን ስለ ቅድስት ቤተክርስትያን ዘብ እንቁም ዛሬ በሰላማዊ ሰልፍ ይህን የጠየቁ ሰዎች ነገ ምን ማድረግ እንደሚያስቡ ለማስረዳት መምህር ሊያሻን አይገባም፡፡

በዚች ምድር ላይ የምንቆየው እንደ ማቱሳላ 969 ዓመት አለመሆኑን አውቀን በኖርንበት፤በምንኖርበት  ጊዜ ሁሉ ከቤተክርስትያን ጎን ለመቆም ያብቃል፡፡